“የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና፣በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!”በሚል መሪ ቃል የወረዳው የመንግስት ሰራተኞች የውይይት መድረክ ተካሄደ!

ጦራ/መስከረም-22/2018 ዓ.ም.ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/”የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!”በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ የመንግስት ሠራተኞች የውይይት መድረክ ተካሄደ!
የውይይት መድረኩ እንደ ሀገር የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን በጋራ ትጋት እንደሚረጋገጥ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ታልሞ የተዘጋጀ መድረክ እንደነበረም በቀረበው የውይይት ሰነድ ተገልፀዋል።
ሀገራችንን ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና በማሸጋገር ብሔራዊ ጥቅማችንን በማስከበር ሂደት ላይ የሁሉም ዜጋ ሚና ከፍተኛ መሆን እንደሚገባም በተካሄደው መድረክ ተገልፀዋል።
የተካሄደው የውይይቱ መድረክ ወቅቱን የጠበቀና አሁናዊ ዓለም ዓቀፋዊ አሁጉራዊና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ለመገንዘብ ያስቻለ ስለመሆኑም የተገለፀ ሲሆን በውይይቱ ሀገር የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ትጋት እንደሚረጋገጥ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
የውስጥ አንድነትን በማጠናከር በህብረት መቆምና ውስጣዊ ሰላምን ማረጋገጥ ለታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና ግንባታ ወሳኝ ስለመሆኑም ተብራርቷል።
አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን፣የመንግስት ተቋማትን በማጠናከር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከስሩ በማረም ተቋማቱን ውጤታማ ለማድረግ መስራት እንደሚገባም ተገልጿል።
ዜጎች የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥና የብልፅግና ጉዞን ለማፋጠን በሀገራዊ ጥቅሞች የማይደራደር ስብዕናን መላበስ እንደሚገባቸውም ተመላክቷል።
የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የተመዘገቡ ድሎችን ማስቀጠልና ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን እና ድሎቻችን ለማፅናት በአንድነት መቆም እንደሚገባ በውይይት መድረኩ የጋራ አቋም ተይዟል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top