የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀቶችን በማጠናከር የሴቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል ተባለ!!

ይህ የተገለጸው የላንፉሮ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በላንፉሮ ወረዳ ጦራ ከተማ በተካሄደው ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ነው፡፡
ጽ/ቤቱ” የላቀ ትጋትና ቅንጅት፤ ለሴቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ዓመታዊ ጉባዔ አካሂደዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የላንፉሮ ወረዳ ረደት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብደላ አህመድ እንደገለፁት የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት የዘርፉ ተቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም በወረዳው በየደረጃው ያሉ የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀቶችን በማጠናከር የሴቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት አቶ አብደላ፡፡
በዘርፉ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦና ተናቦ በቅንጅት በሙሉ አቅም ርብርብ ማድረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
የስልጤ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ መህዲያ አምደላ እንዳሉት የሴቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በየደረጃው ያሉ አደረጃጀቶችን በማጠናከር በመጠቀም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተሰማሩበት ዘርፍ ለህፃናት መብትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት መስራት እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት ስራ አፈፃፀም ሂደት ላይ የታዩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ አንኳር ችግሮችና ተግዳሮቶች አፅንኦት ሰጥተው በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች የትምርህት ቁሳቁስ እንዲሁም በወረዳው በኢንተርፕራይዝ በመስኖ ፣በዶሮ እርባታ እና በሌሎችም የስራ መስኮች ተደራጅተው ውጤታማ ለሆኑ ሴቶች የሰርተፊኬት እውቅና በመስጠት የዕለቱ መርሐግብር ተጠናቋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top