





የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ አስተዳደር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎችና 05 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን ወረዳው በለውጥ ጎዳና ውስጥ ከሚገኙ የዞኑ ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡የወረዳው መቀመጫ ቂልጦ ከተማ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 39ኪሎሜትር ርቀት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ ሆሳዕና በስተ ደቡብ አቅጣጫ 36 ኪ.ሜ እንዲሁም ከአዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ 228ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳው በ17 የገጠር ቀበሌዎች፣በ01 የከተማ ቀበሌና በሶስት ታዳጊ ማዘጋጃ ቤታዊ ከተማ የተዋቀረች ሲሆን በወረዳዋ ከ120 ሺህ በላይ የሚጠጋ የህዝብ ብዛት አለት። በወረዳው የሚገኘው አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የስልጥኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው።በወረዳው የሚገኘው ማህበረሰብ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ይሁን እንጂ የተለያዩ ብሔርና ሃይማኖት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰላምና በፍቅር ተዋደውና ተከባብረው በጋራ የሚኖሩበት፤የአብሮነት: የመቻቻል፣የአንድነት መገለጫ እና በፈጣን ዕድገት ላይ ትገኛለች ።
በተለይም ወረዳዉ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦች መገኛም ናት ከመስህቦቹ መካካል የሀጅአሊዬ መካነ ቀብር፣ የብልጬ ሸለቆ ፣የአህመድ ግራኝ ትክል ድንጋይ የበዋ ጥብቅ ደን፣የእመዣር ዋሻ፣የአብራኖ ፏፏቴ እና ሌሎችም የቱሪስት መስህብ መገኛ ናት።የወረዳው መልከዓ ምድር ወይነደጋና ለም መሬት ያላት;የተለያዩ ምርቶች የሚመርቱበት በመሆኑ ለኑሮ፣ለንግድና ኢንቨስትመንት ለአብነትም በግብርናው ዘርፍ ፦በፍራፍሬ ፦ አቮካዶ እና ፖም ፤ በቅመማ-ቅመም፦ ቡና ኮሰረትና ሮዝመሪ ፤በእንሰሳት ዘርፍ፦ በወተት ሀብት በዶሮ እና በንብ ማነብ ምቹና በባህሪው ወይና ደጋ የአየር ንብረት ያለው እንዲሁም የህዝቡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተደምሮ የወረዳውን ሁለንተናዊ ለውጥ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገርና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን ይህም ወረዳው በሁሉም ዘርፍ ፈጣንና አስተማማኝ መዋቅራዊ ኢኮነሚያዊ ዕድገት እያስመዘገበ በፈጣን ዕድገት መገስገስ እንድችል ትልቅ አቂም መፍጠር ችሏል፡፡ለወረዳው ሁለንትናዊ ለውጥ ይህ የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ይፋዊ የዌብ ሳይት ድህረ ገፅ ተግባራዊ መደረጉ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
